Melkam Zena - All the Ethiopian good news in one site

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሰባኬ ወንጌል ሆነ።

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሰባኬ ወንጌል ሆነ። መጋቤ ሐዲስ ተብሎም ተሰይሞአል። ( በዚህ ጽሑፍ አቅራቢ) ካህናቱና ጳጳሳቱ ወንጌሉን ካላስተማሩን ከምእመናኖቻችን ብንማርስ? ወንጌል በሁለት ዋና ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። የአምላኩን ህግ አፍርሶ ለሞት የተዳረገውን የሰው ልጅ ሊያድን የመጣውን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ማመንና በፍቅር መኖር ናቸው። ስለዚህ ወንጌል በመድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ያላመኑትን አህዛብ አምነው […]

ኢትዮጵያዊትዋ ማርያም?

ኢትዮጵያዊትዋ ማርያም።? ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላሉ የድሮ ሰዎች። ዘንድሮ ደግሞ ሰምቼ የማላውቀውን ጉድ ነው እየሰማሁ ያለሁት። መልካም ነገር ልበለው ወይስ ምን? እርሱን አውቄ ስጨርስ እደመድማለሁ። ከፍያለው ቱፋ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለችው ማርያምና ሰዎች የሚነግዱባት ማርያም የሚለውን የቪዲዮ መልእክት ከለቀቀ በኋላ ሁለት ማርያሞች አሉ እንዴ? የሚል ከባድ ጥያቄ ተፈጠረብኝ። ከዚያም የምችለውን ያህል መጽሐፍ ቅዱሱን ማንበብ ጀመርኩና […]

Abune mathias

Wefe-Gezit ወፈ-ገዝት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ መምህር አሰግድን አወገዙ ሌሎችንም አስጠነቀቁ።

ወፈ- ገዝት፡- የኢትዮጵያው ፓትሪያርክ «አቡነ»  ማቲያስ ጸረ ወንጌሎችን ትተው ወንጌልን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚሰብኩትን አወገዙ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ፓትርያርክም ሆነ እውነተኛ መንፈሳዊ  አባት እንደሌላት ገና ዛሬ ነው በደንብ የገባኝ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መምህር አሰግድን ያወገዙበትንና ሌሎችንም ያስጠነቀቁበትን ቃለ ውግዘት ስሰማ እኚህ ሰውየ ወፈ ገዝት ናቸው እንዴ? ነው […]

ፌቨን አበጋዝ Feven Abegaz

An Ethiopian woman who illegally took more than 9 Million Birr from 8 people has captured ከስምንት ግለሰቦች ከዘጠኝ ሚልዮን ብር በላይ በቼክ እንዳጭበረበረች የተጠረጠረችው የአዋሳ ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች

ዓለም አንድ መንደር እየሆነች የመሄድዋ ሚስጢር ቀጥሎአል። ወንጀለኞች አይደለም በአገር ውስጥ ባለ ጫካ ከአገር ሸሽተውም ማምለጥ አልቻሉም። ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የተሰማው ዜናም የሚያሳየው ይህንን ነው። ወይዘሮ ፌቨን አበጋዝ የተባለች ሴት በአዋሳ ከተማ ከባለቤትዋ ጋር በመተባበር ከስምንት ሰዎች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በቼክ አጭበርብራለች በሚል ጥርጣሬ ስትፈለግ ከአገር ጠፋች። ነገር ግን ለኢትንተር ፖል በተላለፈው የአፋልጉን እርዳታ መሠረት […]

Let us correct our standard መለኪያችንን እናስተካክል።

የተሳሳተ መለኪያና መዘዙ። መለኪያ ሲሳሳት አደገኛ ነው ። የሚለካው ቢሳሳት በመለኪያ ተለክቶ ይስተካከላል። መለኪያ ራሱ ከተሳሳተ ግን በርሱ የሚለካው ነገር ሁሉ የተሳሳተ ልክ ይዞ ይወጣል። ለዚህም ይመስለኛል የጥንት ሰዎች ሲተርቱ «ውሀ ቢያንቅ በምን ይውጡ ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ» የሚሉት። አንድ ሰው ምግብ ትን ቢለው ውሀ ጠጣ ይባላል። ውሀ ጠጥቶ ከሆነ ትን ያለው ግን ምን ይጠጣል? […]

Two Ethiopian priests sentenced to prison for killing a man who beg for money and then attack them ሁለት ቄሶች ለታክሲ ገንዘብ በመጠየቅ የነዘነዛቸውን ሰው በመግደል ተፈረደባቸው።

ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ የተሰማው ዜና ይገርማልም ያሳዝናልም። መስከረም 19 ቀን ቄስ  ሞገስ ዘለቀና ቄስ ፈቃዱ ገብረ ኢየሱስ የተባሉ ቄሶች ከገብርኤል ማህበር ሲመለሱ ምሽት ላይ ሲ ኤም ሲ አያት አደባባይ አካባቢ ሲደርሱ አንድ ሰው በጨለማ ሲከተላቸው ኮቴውን ይሰማሉ። ከዚያም ያ ሰው ቀረብ አለና ለታክሲ የሚሆን ገንዘብ እንዲረዱት ይጠይቃቸዋል። እነርሱ ግን ገንዘብ እንዳልያዙ ነግረውት ጉዞአቸውን ይቀጥላሉ። ሰውየው ግን […]

What is the standard of our braveness? የጀግንነት መለኪያችን ምንድን ነው?

አባቴ ጀግና ነበር። ጀግንነትን በመጀመሪያ ያየሁት በርሱ ነው። ከጀግንነቱ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ነበሩ። አንደኛ ቃሉን በጣም ያከብራል ተናገረ ማለት አደረገ ነው። በዚህ አገሩ ህዝቡ ሁሉ ያውቀዋል። በዚህ ምክንያት ቃሉ ፊርማው የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶት ነበር። አባቴ ፈርም ሳይባል ነው ያለፈው። ቃል ቃል ነው ይላል። ሌላው አባቴ ድሆችን ይረዳል። ያለኝ የኔ ብቻ ነው የሚል እምነት የለውም። […]

የኤምባሲ ፎርጂድ

ብዙ ነገሮች ፎርጂድ ይሰራባቸዋል። ስለዚህ ገንዘብ ስንቀበል ወይም የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ስንገበያይ ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን። ተመሳሳይ እንዳይሆን እንፈራለንና። ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ግን ከዚህም እጅግ ያለፈና የሚገርም ነው። በጋና ውስጥ ፎርጅድ የሆነ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለ ተደርሶበታል። በዚህች አፍሪካዊት አገር ትክክለኛው የአሜሪካ ኤምባሲ ያለ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ ነኝ ብሎ ለብዙዎች ትክክለኛ የአሜሪካ ፓስፖርት ግሪን […]

የኢትዮጵያ ገንዘብ በሚኒሊክ ጊዜ።

ዓፄ ምኒልክ የመጀመሪያዎቹን የብር ኖቶች በህዝብ ዘንድ ቶሎ ተቀባይነት አለማግኘትን አስመልክተው ያስነገሯቸው ፈገግ የሚያደርጉ አዋጆች። ዳግማዊ ዓጼ ምኒሊክ የመጀመሪያዎቹን የመገበያያ ገንዘቦች ወደ ገበያ ባስገቡበት ጊዜ ልክ እንደሌላው ጊዜ ሁሉ በህዝብ ዘንድ አዲስ ነገር ያለመቀበል ፈተና ገጥሟቸው ነበር። ከዚህ በፊት በነበረው ነባር ብር ላይ ያለው የማርትሬዛ መልክ ተለውጦ የምኒልክ መልክ በመተካቱም ህዝቡ ሌላ ገንዘብ እየመሰለው አልገበያይ […]

የአጼ ቴዎድሮስ ደብዳቤ ልውውጥ።

የፕላውዲን ገዳዮች እና የዓጼ ቴዎድሮስ ደብዳቤ በዘመኑ ብዙም የሚሰራው ስራ ባይኖረውም፤ የእንግሊዝ መንግስት በአፄ ቴዎርድሮስ ትመራ በነበርችው ኢትዮጵያ ቆንፅላ አቇቁማ ነበር። የቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊም ዎልተር ቺቺሊ ፕላውዲን ይባል ነበር። የመጀመሪያው ደብዳቤ ዓጼ ቴዎድሮስ የፕላውዲንን ወኪልነት በመቀበል የፃፉት ደብዳቤ ነው። ሚስተር ፕላውዲን በመላክተኛነት በሚያገለግልበት ጊዜ ህመም ያጋጥመውና ህመሙን ለመታከም ወደ አገሩ እንግሊዝ በሚጏዝበት ወቅት ጎንደር […]

  • 1
  • 2