ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የኢትዮጵያ ትምህርት አባት።

ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የኢትዮጵያ ትምህርት አባት።

የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አመሰራረት እና ለተማሪ ቤቱ መቋቋሚያ እርዳታ የሰጡ ሰዎች

ግርማዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ (በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ውራሽና እንደራሴ ልዑል ተፈሪ መኮንን ሲባሉ ሳሉ) አንድ ተማሪ ቤት በ፲፱፻፲፭ (1915) ዓም በዘመናዊ አሰራር አሰናዱ። ትምህርት ቤቱም “ተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት” ተብሎ በስማቸው ተጠራ።
ስለአዳሪዎች ተማሪዎች ለመኝታ የሚሆን ባለ ሶስት ፎቅ አንድ ትልቅ ቤት በ፲፱፻፲፮ (1916) ዓም ተሰራ። በዚህ አመት ዳግመኛ ለተማሪ ቤቱ ግቢ 25 ሄክታር መሬት ተከልሎ ዙሪያው አጥሩ በደንጊያ ካብ ታጠረ።
ለትምህርት ስራ የሚያስፈልጉት መፃህፍትና ልዩ ልዩ ዓይነት መሳሪያዎች ከአውሮፓ እንዲመጡ ትእዛዝ ተደርጎ ነበርና እቃዎቹ በጥር ወር ፲፱፻፲፯ (1917 ) ዓም አ ዲስ አበባ ደረሰ።
ሚያዚያ 19 1917 ዓም ክቡራን ሚኒስትሮች፣ መኳንንትና ወይዛዝር፤ ኮር ዲፕሎሎማቲክና ታላላቅ የውጭ አገር ሰዎች ሁሉ በተገኙበት ልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤቱን መርቀው ከፈቱ።
በዚያ በመጀመሪያው ጊዜያት የአዳሪዎች ተማሪዎች ቁጥር 30 ሲሆን፣ የተመላላሾች ቁጥር 50 አይበልጥም ነበር።
የትምህርት ቤቱ ሃላፊ ዶክተር ክቡር ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ነበሩ
ለተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት መቋቋሚያ እርዳታ የሰጡ ሰዎች ስማቸው የሚከተሉት ነበሩ።

የካቲት 18፣ 1918 ዓም
ልዕልት ወይዘሮ መነን (በኋላ ግርማዊት እቴጌ) ———- 1333 ብር
ክቡር ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (የጦር ሚኒስትር) ——- 300 ብር
ክቡር ደጃዝማች ጌታቸው አባተ ——– 392 ብር 15 መሐለቅ
ክቡር ድጃዝማች ብሩ ወልደ ገብርኤል —– 10 ወቄት ወርቅ
ደጃዝማች ሀብተ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር—– 200 ወቄት ወርቅ
ደጃዝማች አባ ውቃው ————– 300 ብር
ቀኛዝማች ዓምዴ ሀብተ ስላሴ —— 100 ብር
ሙሴ ሌቢስኪ ———————— 50 ብር
ባሻ ወርቄ —————————- 20 ብር
መጋቢት 23፣ 1918 ዓም
ክቡር ራስ ኃይሉ (በኋላ ልዑል የተባሉ) —– 5000 ብር
ክቡር ራስ ከበደ መንገሻ ————— 500 ብር
ክቡር ደጃዝማች ሙሉጌታ (በኋላ ራስ የተባሉ) —– 150 ብር
ፊታውራሪ ዓምዴ ሀብተ ስላሴ —— 60 ብር 62 መሐለቅ
ኮሎኔል ስናፎርድ ——— አንድ ትልቅ ግሎብ ዋጋው 60 ብር
ሙሴ ጳውሎስ በያመቱ 25 የአራት አመት ሂሳብ ፣100 ኪሎ ስኳር፣200 ኩባያ የአሊሚኒየም፣12 ታኒካ ጥሩ ሻይ፣24 ፎጣ
አቶ አስፋው ገሠሠ ዓስራት ——— 50 ብር
ሰኔ 2፣ 1919 ዓም
ልዑል ራስ ጉግሳ አርአያ ————– 500 ብር
ሰኔ 23 ፣ 1919 ዓም
ክቡር ደጃዝማች ብሩ ወልደ ገብርኤል
 10 ወቄት ወርቅ፣10 ጥገት ላም፣100 ወላድ በግ፣3 ጥንድ በሬ
ዲክ ዴዝ አብሩዚ —————– 1000 ብር
ደጃዝማች ሀብተ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር —– 200 ብር

ምንጭ
የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አጭር ታሪክ (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት)

%d bloggers like this: