የአጼ ቴዎድሮስ ደብዳቤ ልውውጥ።

የአጼ ቴዎድሮስ ደብዳቤ ልውውጥ።

የፕላውዲን ገዳዮች እና የዓጼ ቴዎድሮስ ደብዳቤ

በዘመኑ ብዙም የሚሰራው ስራ ባይኖረውም፤ የእንግሊዝ መንግስት በአፄ ቴዎርድሮስ ትመራ በነበርችው ኢትዮጵያ ቆንፅላ አቇቁማ ነበር። የቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊም ዎልተር ቺቺሊ ፕላውዲን ይባል ነበር። የመጀመሪያው ደብዳቤ ዓጼ ቴዎድሮስ የፕላውዲንን ወኪልነት በመቀበል የፃፉት ደብዳቤ ነው።
ሚስተር ፕላውዲን በመላክተኛነት በሚያገለግልበት ጊዜ ህመም ያጋጥመውና ህመሙን ለመታከም ወደ አገሩ እንግሊዝ በሚጏዝበት ወቅት ጎንደር ከተማ ኣጠገብ ቀሃ ከሚባለው ወንዝ ሲደርስ በድንገት የደጃች ጋረድ ሰዎች ደርሰው ደረቱ ላይ በጦር ወጉት፤ ማርከውም ወሰዱት። ዓጼ ቴዎድሮስም ከማራኪዎቹ ጋር በተደረገው ድርድር መሰረት አንድ ሺህ ብር ከፍለው ፕላውዲንን አስለቀቁት። ሆኖም ግን ፕላውዲን ክፉኛ ቆስሎ ስለነበር ለዘጠኝ ቀናት በህመም ሲሰቃይ ቆይቶ በጥር ወር ፲፰፻፶፫ ዓም (1853) ሞተ። ፕላውዲንም ነገስታት ከሚቀበሩበት ቦታ ተቀበረ። ይህ የግድያ ተግባር ዓጼ ቴዎድሮስን ለበቀል አነሳሳቸው እናም ጋረድን እና ጭፍራዎቹን ካጠፉ በሇላ የሚቀጥለውን ደብዳቤ ፕላውዲንን ተክቶ ሲሰራ ለነበረው ለራፋዔል ባሮኒ ፃፉ።
ምንጭ:
አጤ ቴዎድሮስ
በጳውሎስ ኞኞ

%d bloggers like this: