የኤምባሲ ፎርጂድ

የኤምባሲ ፎርጂድ

ብዙ ነገሮች ፎርጂድ ይሰራባቸዋል። ስለዚህ ገንዘብ ስንቀበል ወይም የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ስንገበያይ ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን። ተመሳሳይ እንዳይሆን እንፈራለንና። ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ግን ከዚህም እጅግ ያለፈና የሚገርም ነው። በጋና ውስጥ ፎርጅድ የሆነ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለ ተደርሶበታል። በዚህች አፍሪካዊት አገር ትክክለኛው የአሜሪካ ኤምባሲ ያለ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ ነኝ ብሎ ለብዙዎች ትክክለኛ የአሜሪካ ፓስፖርት ግሪን ካርድና ሰነዶች ሲሰጥ የነበረ የተሳሳተ ኤምባሲ ተገኝቶአል። ይህ ኤምባሲ  ያልሆነ ኤምባሲ የሚሰጣቸው ዶኪመንቶች በህገ ወጥ መንገድ ከስቴት ዲፓርትመንት የወጡ ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ ብዙዎችን ወደ አሜሪካ አሻግሮአል። እኔን ያሳሰበኝ የነዚህ ትክክለኛ መስሎአቸው የመጡ ሰዎች ሲሆን ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

%d bloggers like this: