የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ አረፉ

የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ አረፉ

ታላቋንና ገናናዋን አገር አሜሪካን በመቋቋም የሚታወቁት የእድሜ ባለጸጋው ፊደል ካስትሮ በዘጠና ዓመት እድሜአቸው በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሜሪካ አፍንጫ ስር ሆነው ለገናናዋ አገር አልንበረከክም በማለት የሚታወቁት ፊደል ካስትሮ ረጅሙን እድሜ ጠግበዋል። በርሳቸው ቦታ ተተክተው አገሪቱን እየመሩ ያሉት ታናሽ ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ሲሆን ከርሳቸው ይልቅ ለስለስ ያሉ ይመስላሉ። የተለያዩ የአገር መሪዎች የካስትሮን መሞት አስመልክተው በሚያስተላልፉአቸው ዜናዎች የተለያየ ስሜት እያንጸባረቁ ሲሆን አንዳንዶቹ በመሞታቸው የተደሰቱ ይመስላሉ ሌሎቹ ደግሞ ሰብአዊ ኃዘናቸውን በመግለጽ ለኩባ ህዝብ ኃዘናቸውን አስተላልፈዋል። ከሁሉም የሚገርመው አዲሱ ተመራጭና ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተራቸው ያስተላለፉት አጭር መልእክት ሲሆን «ፊደል ካስትሮ ሞተዋል» የሚል በቃለ አጋኖ የታጀበ መልእክት ነው። ቃለ አጋኖው እና አጭሩ መልእክታቸው በመሞታቸው ቅር እንዳልተሰኙ የሚያሳይ ነው ተብሎ ተተርጉሞአል። የኚህ ስመ ገናና ሰው መሞት  ለሁላችንም የሚያስተላልፈው አንድ መልእክት ቢኖር ሁሉም አላፊ መሆኑን ይመስለኛል። በጣም የገነኑና የማያልፉ የሚመስሉ ነገሮች ሁሉ ጊዜን ጠብቀው ያልፋሉ። ጊዜ የሁላችንም ባለውለታና የማያዳላ ዳኛ ነው።

%d bloggers like this: