ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። Doctor Abiy becomes next Ethiopian PM

Doctor Abiy

ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። Doctor Abiy becomes next Ethiopian PM

በመልካምና ጥበብን በተሞላ ንግግራቸው የብዙዎችን ልብ የነኩትና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኙት ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። በሚያቀርቡአቸው አንድነትን ሰላምን በሚያጎሉ የጥበብ ንግግሮቻቸው በቅርቡ እየታወቁ የመጡት ዶክተር አቢይ ያለ እድሜአቸው የበሰሉ የጎልማሳ አዋቂ መሆናቸውን ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል። ዶክተር አቢይ በተለይ በአሁኑ ጊዜ መመረጣቸው ኢትዮጵያ ካለችበት ሁኔታ አንጻር መልካም ሲታይ በጣም በጎና አወንታዊ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል። ለዚህም ምክንያቱ ሰውየው በጎ አስተሳሰብ ያላቸው ትሁትና ለመሪነትና የሚያበቃ ስብእና ያላቸው ሰው በመሆናቸው ህብረተሰቡን ከማቀራረብ አንጻር ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ስለሚታመን ነው። እኛም ለዶክተር አቢይ መልካም የስኬት ስልጣን ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

%d bloggers like this: