Archive: 'Nov 2016' :

Echo የገደል ማሚቶ አዙሪት።

ገደል ማሚቶ  THE POLITICS OF REACTION(S) ሰው የተፈጠረው ማሰብ ማቀድ መስራት የሚችል ፍጡር ሆኖ ነው። ሰው ይህን የተፈጥሮ ችሎታውን በመጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ያስባል ያቅዳል ይፈጥራል። በውስጡ ያለው ይህ ችሎታ በሁለት መንገድ ይጠቀምበታል። የሚፈልገውን ነገር አቅዶ አስቦ ወደ ውጤት ለማምጣትና እውን ለማድረግ (Pro-action) ሁለተኛ ደግሞ ለሚገጥሙት ነገሮች ምላሽ ለመስጠት ነው። (Re-actions) ለምሳሌ አንድ […]

አንዲት ሴት ከአውሮፕላን ላይ ዘላ ወረደች።

ነገሩ የተከሰተው በትናንትናው እለት በሒውስቶን ከተማ ሲሆን አንዲት ከሉዚያና ግዛት በዩናይትድ ኤርላይን ተሳፍራ የመጣች ሴት አውሮፕላኑ ገና በማኮብኮብ ላይ እያለ የአደጋ መውጫ በሩን ከፍታ በመውጣት ወደ ተከለከለው ስፍራ ሮጣለች። የሴትዮዋ ጤንነነትና ለምን እንዳደረገችው በፖሊስ እየተጣራ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም በኩባው መሪ ሞት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጡ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቀድሞው የኩባ መሪ ካስትሮ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ  በላኩት የሀዘን መግለጫ  ፊደል ካስትሮ በችግር ጊዜ  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ ታላቅ  እና መሪ ነበሩ፤ ብለዋል ። በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዳለ በመግለጽ ለኩባ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል። ምንጭ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ አረፉ

ታላቋንና ገናናዋን አገር አሜሪካን በመቋቋም የሚታወቁት የእድሜ ባለጸጋው ፊደል ካስትሮ በዘጠና ዓመት እድሜአቸው በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሜሪካ አፍንጫ ስር ሆነው ለገናናዋ አገር አልንበረከክም በማለት የሚታወቁት ፊደል ካስትሮ ረጅሙን እድሜ ጠግበዋል። በርሳቸው ቦታ ተተክተው አገሪቱን እየመሩ ያሉት ታናሽ ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ሲሆን ከርሳቸው ይልቅ ለስለስ ያሉ ይመስላሉ። የተለያዩ የአገር መሪዎች የካስትሮን መሞት አስመልክተው […]

THE REASON BEHIND THE REASON OF THE CURRENT ETHIOPIAN PROBLEM

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ እየታዩ ካሉት ችግሮች ጀርባ ያለ እውነተኛ ምክንያት። ከብዙ ምክንያቶች ጀርባ ያለ አንድ ምክንያት የአንድን  ችግር ምንጭ ማወቅ የችግሩ ግማሽ መፍትሄ ነው ይባላል። የችግርን ምንጭ ማወቅ እንዴት መፍትሄ ይሆናል ለሚል ሰው መፍትሄው የችግሩን ምንጭ ማወቃችን ራሱ ሳይሆን የችግሩን ምንጭ ማወቃችን ትክክለኛውን መፍትሄ እንድናገኝ ስለሚረዳን ነው። የማንኛውንም ችግር ምንጭ ካላወቅን ያልተቀደደ ስንሰፋ የማያድን […]

MESSAGE OF PEACE FOR ETHIOPIANS

ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያ መንግስት ያለኝ መልእክት። አንድ ኢትዮጵያዊ ተራ ዜጋ ነኝ። በአገሬ ጉዳይ ላይ ብዙም ድምጼን አሰምቼ  አላውቅም። አሁን በዚህ ወቅት ላይ እየሆነና እየተባለ ያለው ነገር ግን እንደ አንድ ዜግነቴም ቢሆን ድምፄን ማሰማት አለብኝ ብየ እንድነሳ አስገድዶኛል። በአሁኑ ወቅት ከመልካሙ ነገር ይልቅ ክፉው ነገር ጎልቶ እየተሰማ ያለ ይመስላል። የሰላም የፍቅር የአንድነት ድምጾች በክፉ ድምጾች እየተዋጡ […]

Back to the basic ወደ መሠረታችን እንመለስ

ወደ መሠረታችን እንመለስ አራቱን የሂሳብ ህገጋት ሳናውቅ ወይን አልፈን የትም መሄድ አንችልም። አራቱ የሂሳብ ህገጋት የስልጣኔ ሀሁ ናቸው። ይህ የሚታየው ስልጣኔ ሁሉ የተነሳውና የተመሰረተው በነዚህ ቀላል በሚመስሉ የሂሳብ ህገጋት ነው። ሰው ወደ ጨረቃ የወጣው ከነዚህ ተነስቶ ነው። እርግጥ ነው ማቲማቲክሱ እየተወሳሰበ እየመሰጠረ ይሄዳል  ቢሆንም በሩ ይህ ነው። በዚህ በር ያልገባ የትም አይደርስም። ጋን በጠጠር ይቆማል […]