Category Archive: 'News'

Doctor Abey Ahmed

የኢትዮጵያን ሕዝብ ትክክለኛ ችግር የሚያወቁና መፍትሄውን የሚጠቁሙ ሰው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተመርጠዋል። ለመሆኑ ህዝቡ ይቀባላቸው ይሆን??

አንድ ጺማቸው  በጣም በጣም ብዙና ረጅም ጺም የነበራቸው መነኩሴ ነበሩ ይባላል። እኚህ አባት አንድ ጥሩ ያልሆነ ጠረን እየሸተታቸው ይቸገሩና ተማሪዎቻቸውን እባካችሁ አንድ ነገር ይሸተኛል ፈልጋችሁ አስወግዱልኝ ብለው ይጠይቃሉ። ተማሪዎችም ያንን መልካም ያልሆነ ጠረን ምንጭ ቢፈልጉ ቢፈልጉ ያጡታል። በመጨረሻም አባ ተቸገሩና ግራ በመጋባት ጺማቸውን አሸት ዳበስ ሲያደርጉ አንድ ነገር ጠጠር ይልባቸዋል። ጺማቸውን ስርስር አድርገው ሲያወጡት ከትናንት […]

Doctor Abiy

ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። Doctor Abiy becomes next Ethiopian PM

በመልካምና ጥበብን በተሞላ ንግግራቸው የብዙዎችን ልብ የነኩትና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኙት ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። በሚያቀርቡአቸው አንድነትን ሰላምን በሚያጎሉ የጥበብ ንግግሮቻቸው በቅርቡ እየታወቁ የመጡት ዶክተር አቢይ ያለ እድሜአቸው የበሰሉ የጎልማሳ አዋቂ መሆናቸውን ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል። ዶክተር አቢይ በተለይ በአሁኑ ጊዜ መመረጣቸው ኢትዮጵያ ካለችበት ሁኔታ አንጻር መልካም ሲታይ በጣም በጎና አወንታዊ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል። […]

ኢትዮጵያ እንደገና መልካም መሪ ልታገኝ ደጃፍ ላይ የደረሰች ይመስላል።

መልካም ዜና ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን የሰማን እለት በጣም ነበር ያዘንነው። መንግሥት የተለያዩ ጉድለቶች ቢኖሩበትም እርሳቸው ግን መልካምና ቀና መሪ ነበሩና። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ እንደገና መልካም መሪ ልታገኝ ደጃፍ ላይ የደረሰች ይመስላል።  ስለዚህ ኃዘናችን ወደ ደስታ ስሜት እየተለወጠ ነው። መቸም ከተወሰኑ በጥላቻ ብቻ ከተሞሉና እነርሱ ስልጣን ካልያዙ ወይም አገር ካልተበጠበች ከማይረኩ […]

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን መልቀቅ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስልጣን መልቀቅ እንደሚፈልጉ ዛሬ ማታ ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር አስታወቁ። ኢትዮጵያ እንደገና በለውጥ ሂደት ያለች ይመስላል። እኔን የሚገርመኝ ግን ስንለውጥ ወደ ባሰ ሳይሆን ወደ ተሻለ የምንለውጠው መቼ ይሆን? ያ እንደዛሬው በስሜት ተነሳስቶ ንጉሡን ከስልጣን አውርዶ የገደለው የስድሳዎቹ ለውጥ ከንጉሡ የተሻለ መልካም ነገር አመጣን? ከዚያ በኋላ ይከው እስከ ዛሬ ድረስ ለአርባ […]

ፌቨን አበጋዝ Feven Abegaz

An Ethiopian woman who illegally took more than 9 Million Birr from 8 people has captured ከስምንት ግለሰቦች ከዘጠኝ ሚልዮን ብር በላይ በቼክ እንዳጭበረበረች የተጠረጠረችው የአዋሳ ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች

ዓለም አንድ መንደር እየሆነች የመሄድዋ ሚስጢር ቀጥሎአል። ወንጀለኞች አይደለም በአገር ውስጥ ባለ ጫካ ከአገር ሸሽተውም ማምለጥ አልቻሉም። ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የተሰማው ዜናም የሚያሳየው ይህንን ነው። ወይዘሮ ፌቨን አበጋዝ የተባለች ሴት በአዋሳ ከተማ ከባለቤትዋ ጋር በመተባበር ከስምንት ሰዎች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በቼክ አጭበርብራለች በሚል ጥርጣሬ ስትፈለግ ከአገር ጠፋች። ነገር ግን ለኢትንተር ፖል በተላለፈው የአፋልጉን እርዳታ መሠረት […]

Two Ethiopian priests sentenced to prison for killing a man who beg for money and then attack them ሁለት ቄሶች ለታክሲ ገንዘብ በመጠየቅ የነዘነዛቸውን ሰው በመግደል ተፈረደባቸው።

ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ የተሰማው ዜና ይገርማልም ያሳዝናልም። መስከረም 19 ቀን ቄስ  ሞገስ ዘለቀና ቄስ ፈቃዱ ገብረ ኢየሱስ የተባሉ ቄሶች ከገብርኤል ማህበር ሲመለሱ ምሽት ላይ ሲ ኤም ሲ አያት አደባባይ አካባቢ ሲደርሱ አንድ ሰው በጨለማ ሲከተላቸው ኮቴውን ይሰማሉ። ከዚያም ያ ሰው ቀረብ አለና ለታክሲ የሚሆን ገንዘብ እንዲረዱት ይጠይቃቸዋል። እነርሱ ግን ገንዘብ እንዳልያዙ ነግረውት ጉዞአቸውን ይቀጥላሉ። ሰውየው ግን […]

የኤምባሲ ፎርጂድ

ብዙ ነገሮች ፎርጂድ ይሰራባቸዋል። ስለዚህ ገንዘብ ስንቀበል ወይም የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ስንገበያይ ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን። ተመሳሳይ እንዳይሆን እንፈራለንና። ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ግን ከዚህም እጅግ ያለፈና የሚገርም ነው። በጋና ውስጥ ፎርጅድ የሆነ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለ ተደርሶበታል። በዚህች አፍሪካዊት አገር ትክክለኛው የአሜሪካ ኤምባሲ ያለ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ ነኝ ብሎ ለብዙዎች ትክክለኛ የአሜሪካ ፓስፖርት ግሪን […]

Echo የገደል ማሚቶ አዙሪት።

ገደል ማሚቶ  THE POLITICS OF REACTION(S) ሰው የተፈጠረው ማሰብ ማቀድ መስራት የሚችል ፍጡር ሆኖ ነው። ሰው ይህን የተፈጥሮ ችሎታውን በመጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ያስባል ያቅዳል ይፈጥራል። በውስጡ ያለው ይህ ችሎታ በሁለት መንገድ ይጠቀምበታል። የሚፈልገውን ነገር አቅዶ አስቦ ወደ ውጤት ለማምጣትና እውን ለማድረግ (Pro-action) ሁለተኛ ደግሞ ለሚገጥሙት ነገሮች ምላሽ ለመስጠት ነው። (Re-actions) ለምሳሌ አንድ […]

አንዲት ሴት ከአውሮፕላን ላይ ዘላ ወረደች።

ነገሩ የተከሰተው በትናንትናው እለት በሒውስቶን ከተማ ሲሆን አንዲት ከሉዚያና ግዛት በዩናይትድ ኤርላይን ተሳፍራ የመጣች ሴት አውሮፕላኑ ገና በማኮብኮብ ላይ እያለ የአደጋ መውጫ በሩን ከፍታ በመውጣት ወደ ተከለከለው ስፍራ ሮጣለች። የሴትዮዋ ጤንነነትና ለምን እንዳደረገችው በፖሊስ እየተጣራ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም በኩባው መሪ ሞት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጡ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቀድሞው የኩባ መሪ ካስትሮ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ  በላኩት የሀዘን መግለጫ  ፊደል ካስትሮ በችግር ጊዜ  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ ታላቅ  እና መሪ ነበሩ፤ ብለዋል ። በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዳለ በመግለጽ ለኩባ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል። ምንጭ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

  • 1
  • 2